አንዳንዶች
ለውጥ በመሪነት ውስጥ ያለውን ዋነኛ ቦታ በመረዳት መሪነት ማለት ለውጥን መምራት ነው ይላሉ ። አንድን ለውጥ መምራት የራሱ የሆኑ
አካሄዶችና መስመሮች ያሉት ተግባር ነው ። አንድ መሪ በመሪነት ዘመኑ ለውጥ የማይቀር ጉዳይ በመሆኑ በዛ የለውጥ ጊዜ በሀላፊነት
ስለሚቆይ ለውጡ የሚያስከትለውን አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ጎኖች መረዳት አለበት ።
በዋናነት
ለውጥ ከሁለት አቅጣጫ የሚመጣ ነገር ሲሆን ፤ ከላይ ወደ ታች ወይም ከታች ወደ ላይ ሊመጣ ይችላል ።ከላይ ወደ ታች የሚመጣው ለውጥ
በመሪዎች ተነሳሽነት የሚጀመር ሲሆን ፤ ከታች ወደ ላይ የሚመጣው ለውጥ ደግሞ በተከታዮች ተነሳሽነት የሚመጣ ነው ። ለምሳሌ በአገር
ደረጃ የሚመጡ ለውጦች ከላይ ባሉ መሪዎች የሚደረጉ ሲሆኑ ይችላሉ ፣ ለምሳሌ በጃፓን አገር ፊውዳሎች መሬታቸውን በፈቃደኝነታቸው
ለጭሰኞቹ በመልቀቅ ያለ ስር ነቀል አብዮት ለውጥን ማምጣት ችለዋል ።
በአንድ
ድርጅት ውስጥም እንዲሁ የበላይ አመራሩ ለውጥን ሊያነሳሳ እና ሊያቅድ ይችላል ። ይህም ብዙሀኑ የማያዩትን ዋናውን ስእል በመረዳት
መሆን አለበት ። ይህም ግራንድ ስትራቴጂ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ፣ ለብዙሀኑ ግልፅ ያልሆነውን በማየት መሪው እቅድ ሊያወጣና ሊመራ
ወደ ሚፈልገው ወደ ዋናው መንገድ ሊመራ ያስችለዋል ።
ለውጥ
ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ተቋማትንና ኩባንያዎች በየጊዜው የሚከናወን ድርጊት ሊያጋጥም የሚችል ነው ፣ ለምሳሌ ኢስትማን ኮዳክ የተባለው የፎቶ ፊልም አምራች
ኩባንያ ቴክኖሎጂው ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ተቀይሮ ከዛ ጋር ራሱን ባለማስማማቱ ከዘመኑ የዲጂታል ፎቶ ግራፍ ቴክኖሎጂ ጋር ሊወዳደር
ባለመቻሉ ለኪሳራ በመዳረግ መክሰሩን ይፋ በማድረግ የመንግስትን ድጋፍ ለመጠየቅ ተገዷል በአንፃሩ ፉጂ የተባለው የጃፓኑ የፎቶ ፊልሞችም
አምራች ኩባንያ በጊዜ ራሱን በተወሰነ ደረጃ ከዘመኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር
በማስማማቱ ህልውናውን ማስጠበቅ ችሏል ።
የፖለቲካ
ታዛቢዎች እንደሚገልፁት «አዲስ ስርአትን ከመመስረት የበለጠ አደገኛ ነገር የለም» ድንገተኛና ያልተጠበቀ ለውጥ በሰዎች ስነ -
ልቦና ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅእኖዎች ከባድ መሆናቸውን በመረዳት ነው ። ሌላው መሪው ለውጥ የሚያስፈልጋቸውንና የማያስፈልጋቸውን
ነገሮችን በቅጡ መለየት አለበት ፣ አንዳንዶች የለውጥን በሰዎች ህይወትና አስተሳሰብ ውስጥ የሚፈጥረውን ስሜት ባለመረዳት ጥሩ ሀሳቦችን
ፀንሰው ነገር ግን ለውጡን እንዴት መምራት እንዳለባቸው ማወቅ ባለመቻላቸው የታሰቡ ታላላቅ ነገሮች የትም ሳይደርሱ ቀርተዋል ።
ለውጥን
ለማካሄድ ነባሮቹም ሆኑ አዲስ መሪዎች በሁለት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸው አይቀሬ ነው ። ለምሳሌ የሀገር መሪ ቢሆንየተወሰነ ለውጥ
ቢደረግ ፣ ህዝቡ ተጨማሪ ሊጠይቅና የተጀመረው ለውጥ እንዲቀጥል ሊፈልግ
ይችላል ፣ የዚህ አይነት ፍላጎት ካለ ያለው ወቅታዊ የሆነው ነባራዊ ሁኔታ ዘላቂ እንዳልሆነ መገመት ይቻላል ። የተጀመረው ለውጥ
እንዲቀጥልና ህዝቡ ሲፈልግ በአንፃሩ ደግሞ ፣ መሪው ለውጡን ከገፋበት የመሪው ስልጣን መሸርሸርንና ብሎም መጥፋትን ያስከትላል ብሎ
ራሱ መሪው ሊሰጋ ሲችል ስለዚህ ያለው አማራጭ ምንም አይነት ለውጥን አለማድረግን እንደ አንድ አማራጭ አድርጎ መሪው ሊሰወስደው
ይችላል ። ይሄም ግን በራሱ አደጋ አለው ፣ ይኀውም ለውጥ በሚያስፈልግበት ሁኔታ ምንም አይነት ማሻሻያን ሳይወስድ መሪው ዝም ብሎ
ጊዜውን ሳይጠቀም ቢቀርና የለውጥ ፍላጎት ገፍቶ ቢወጣ ፣ መሪው ጊዜው ካለፈ በኋላ እንዲነቃና ስርአቱን ማዳን የማይችልበት ሁኔታንና
አብዮትን እሚጋብዝበት ደረጃ ሊደርስና ሲችል መሪው ዘግይቶ በሚነቃበት ወቅት ጊዜው ሊያልፍ ይችላል ።
ነባር
መሪዎች ለውጥን ለማካሄድ ቢሞክሩም ፣ ነገር ግን ለመልካም ለውጥ ብለው የጀመሩት ነገር ሀዲዱን ስቶ ሁሉን ነገር አፈራርሶና ንዶት
ቁጭ ሊል ይችላል ። የቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት ፕሬዝዳንት ጎርባቾቭ ምንም እንኳን በአለም መድረክ ላይ ከምራባውያን ጋር መወዳደር
እያቃተው የነበረውን የሶቭየት ህብረትን ስርአትን ጥገናዊ ለውጥን ለማድረግ የተነሱቢሆንም ፣ ጅምራቸው ባልተጠበቀ አቅጣጫ ሄዶ የሶቭየት
ህብረትን ኮሚኒስታዊ አስተዳዳር ጨርሶ ሊያፈራርሰው በቅቷል ።
አዲስ
መሪዎችም ተመሳሳይ አጣብቂኝ ውስጥ ራሳቸውን ሊያገኙት ይችላሉ ፤ በአንድ በኩል ከእነሱ ቀድሞ የነበረው መሪ የሄደበትን መንገድ
በተወሰነ ደረጃ መለወጥና ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ሊረዱ ሲችሉ እምን ደረጃ ድረስ ነው ለውጥን እሚያካሂዱት የሚለው ራሱን የቻለ
እውቀትን ይጠይቃል ። እነሱም ቢሆኑ ለውጥ ማድረግ ስልጣናችንን ሊሸረሽር ይችላል ብለው ካሰቡ ፣ ምንም ሳያደርጉ ቁጭ ሊሉ ይችላሉ
። ጊዜ እያለፈ በሄደ ቁጥርም በዚህ ምክንያት በቀድሞው መሪ ላይ ጭምር የነበረው ቅሬታ ፣ በጣም በመረረ ሁኔታ ሊመጣባቸው ይችላል ።
በአረቡ
አመፅ ወቅት በሶሪያ መሪ በአሳድ ላይ የተነሳው ተቃውሞ ለበርካታ አመታት በአባትየው ዘመን የነበረው ቅሬታ ጭምር የተገለፀበት ነው ። ልጅየው አሳድ ከአባቱ አሳድ የወረሰውን
አስተዳደር ለውጦችንና ማሻሻያዎችን ለማድረግ ጊዜ የነበረው ቢሆንም ምንም ለውጥ ሳያደርግ በመቆየቱ ከቁጥጥር ውጪ የወጣ ህዝባዊ
አመፅ ሊቀሰቀስና ስርአቱ ሊያከትምለት በቅቷል ። በሌሎችም የአረብ አገራትም እ.ኤ.አ. በ2012 የተነሱት ህዝባዊ አመፆችና ተቃውሞዎች
የዚሁ የለውጥ አስፈላጊነት የቀሰቀሳቸው ናቸው ።
ከመፅሀፍ
ቅዱስ ታሪክ ብንወሰድ ጠቢቡ ሰለሞን ከሞተ በኋላ የስልጣን ወራሹ ለነበረው ለልጁ ለሮአብም ዘመን ተገዢዎቹ ቀንበሩ መረረን ፣ እና
አቅልልን ሲሉ ይጠይቁታል ። ነገር ግን ሮአብም ከአባቴ በበለጠ እጨቁናችኋለሁ በማለቱ ለእስራኤል ለሁለት መከፈልና ለእርስ በእርስ
ጦርነት ተዳርገዋል ። በተለይ ተተኪዎች በለውጥ በኩል ጠንቃቃ መሆን ይገባቸዋል ። ምክንያቱም በቦታው አዲስ በመሆናቸው ፣ ከቀድሞው
ተተኪ እንደመሆ ናቸውና በቀድሞው መሪ ዘመን የመጨቆን ስሜት የሚሰማው ህዝብ ወይንም ተከታያቸው አንድ አይነት ለውጥን ከነሱ መጠበቁ
አይቀርም ።
ለውጥን
መቋቋም ወይም እምቢ ባይነት (Resistance) በራሱ
በመሪውም በኩል ሊመጣ ይችላል ። መሪው በዙሪያውና በስሩ ያለውን እውነታ ካለመረዳት የተነሳ ያንን ለውጥ ላይረዳው ይችላል ። ራሱም
ለውጥን ላለመቀበል ሊያንገራግር ወይም እምቢ ሊል ይችላል።ለውጡ ራሱ ስልጣኔን ያሳጣኛል በሚል ፣ ወይም ለውጡ ያለኝን ነገር ሀብት
ወይም ስልጣን ሊያሳጣ ይችላል ።
ለውጥን
ማድረግ ራሱ የተቋሙ አይነት ይወስነዋል ለምሳሌ ፤ የቻይና መሪዎች ምንም እንኳን ቢለዋወጡም ለውጥን አድርገው ሊከተል የሚችለውን አደጋ ለመጋፈጥ ራሳቸውን
ሪስክ ለመውሰድ ፈቃደኞች አይደሉም ። ይህ ግን ውሎ አድሮ በጣም መሰረታዊ በሆነ ሁኔታ ወደ ስር-ነቀል ልውጥ አብዮት ሊያመራ ይችላል
ህዝቡ ዝም ብሎ የመሪዎች መለዋወጥ ብቻ ከሆነና መሰረታዊ ለውጥ እንደማይመጣ ሲረዳና ተስፋ መቁረጥ ሲጀምር ። በአንፃሩ እንደ አሜሪካ
ባሉ ዲሞክራሲያዊ ስርአቶች ውስጥ ግን መሪዎች በምርጫ ሲለወጡ ለውጥን ማምጣት ቀላል ይሆንላቸዋል ። ለዚህም ምክንያቱ ራሱ ፕሬዝዳንቱም
ሆኑ ሌሎቹ የህዝብ ተመራጮች ለመመረጥ የቀድሞውን መሪ ፖሊሲን ለመለወጥ ቃል ገብተው ስለሆነ ፣ እንደተመረጡ የገቡትንና ህዝቡም
የሚጠብቀውን ቃል በቀላሉ መፈፀም ይችላሉ ። ለምሳሌ ግብር እቀንሳለሁ ብሎ ቃል ከገባ ፣ ወይም ከዚህ አገር ጦር ሰራዊት አስወጣለሁ
የገባውን ቃል መፈፀም ይችላል ።
በጦርነት
ወቅት ለውጥን ማካሄድ እጅግ ፈታኝ ነው ። ለምሳሌ ብዙ ጦርነትን የጀመሩ መሪዎች የሚጨርሱት እነሱ ሳይሆኑ ከእነሱ በኋላ የሚመጡ
መሪዎች ናቸው ያን ጦርነት እንዲያበቃ የሚያደርጉት ። ለምሳሌ አሜሪካ በኢራቅም ሆነ በቬትናም ጦርነት ወቅት ጦርነቱን የጀመሩትምንም
እንኳንበፕሬዝዳንት ኬኔዲ ይመሩ የነበሩት ዲሞክራቶች የነበሩ ቢሆንም ጦርነቱን ያስቆሙት ተቃናቃኝ ከነበረው ፓርቲ ከሪፐብሊካን መሪዎች
ሲሆኑ ፣ በኢራቅ ጦርነትም ወቅት ፕሬዝዳንት አሜሪካ ኢራቅ ውስጥ ከባድ መስዋእትነትን እየከፈለችበት በነበረበት ወቅት ከኢራቅ የእንውጣና
ጦርነቱ እንዲቆም ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ጦርነቱ ለማስቆምም ሆነ ወታደሮቻቸውን ከኢራቅ ለማስወጣት ፈቃደኛ አልነበሩም ። እርሳቸው
ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ፣ የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታንና ከኢራቅ አስወጣለሁ የሚል ቃልን ገብተው በተመረጡት በአዲሱ ፕሬዝዳንት
አሜሪካ ከኢራቅም ሆነ ከአፍጋኒስታን ጦርነቶች ልትወጣ በቅታለች። ይህም የሚፈጥረው የእልህና የስሜታዊተነት የበላይ አመራሩና መሪዎቹ
እስካልተለወጡ ድረስ የፖሊሲ ለውጥን ማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ ነው ።
የጃፓኖች
የአመራር ስልት ካይዘን ማለት ቀጣይና ያልተቋረጠ ለውጥን ማድረግ ማለት ነው ። ይህም የዚሁ የለውጥን አስፈላጊነት የተረዳና ለውጥን
ማስቀጠልንና ማካሄድን ለማመልከት ነው ። በሀገራችንም እንዲሁ የዚህ አስተዳደር አይነት በተለያዩ ድርጅቶች ተግባራዊ መደረግ የጀመረ
ሲሆን ። ይህም ከምእራቡ አለም የኮርፖሬት አስተዳዳር አይነት ለየት ያለ ነው ። እንደ ቶዮታን የመሳሰሉ ግዙፍ የጃፓን ኮርፖሬሽኖች
የሚመሩበት እና ስኬታማ የሆነው ይኀው የአስተዳደር ዘዴ ነው ።
ዝርዝር
አፈፃፀሞችን ለመረዳት መሞከርና መከታተል አንዱ አስፈላጊ የመሪነት ችሎታ ነው ። የነገሮችን ሂደት አስቀድሞ ማየት መቻል ከፍተኛ
ጠቀሜታ ይኖረዋል ልክ በጥንታዊ የግሪክ ተረቶች እንደተጠቀሰው አማልክትና መላእክት ገና ያልደረሰውን ነገር አስቀድመው ያያሉ ብለው
ያምናሉ ። ይህም ሊመጣ የሚችለውን እና የሚያስፈልገውን ለውጥ ለማቀድ ይረዳዋል ።
ብዙውን ጊዜ መሪዎች ስህተት የሚሰሩት በድል ወቅት ነው ። በድል ወቅት
በሚፈጠር ከልክ ያለፈ የራስ መተማመን ስሜትና የአልበገሬነት ስሜት በመገፋፋት ስሜታዊ የሆነ እርምጃን ፣ እንዲሁም አለአግባብ ሌሎችን የሚያስቀይሙ ፣ በቀላሉ ከሌሎች አእምሮ ሊፋቁ የማይችሉ
ቃላትን ሊናገሩ ይችላሉ ።ንግግሮችን ሊናገሩ ይችላሉ ።
አንድ
መሪ ከተከታዮቹ ወይም ከህዝቡ የሚያገኘውን ድጋፍ ለሁልግዜውም እንደሚያገኘው አድርጎ (For Granted) መውሰድ
የሌለበት ሲሆን ፣ የተከታዮቹንም ሆነ የህዝብን ድጋፍ እሚያገኘው በትክክለኛው መንገድ እስከመራ ድረስ ብቻ ነው ። ከዛ ውጪ ግን
በተሳሳተ ጎዳና ከሄደ ያገኝ የነበረውን ድጋፍ ያለምንም ጥርጥር ያጣል ። ለምሳሌ የፈረንሳይን አብዮትን ብንወስድ የፈረንሳይ ህዝብ
ነገስታቱን እጅግ የሚያከብርና የሚወድ ህዝብ እንደሆነ ይነገርለታል ። ነገር ግን ከሉዊስ 14ኛ በኋላ የተነሱት የሉዊስ 14ኛ ልጆችና
የልጅ ልጆች እጅግ የሚከበረውንና የሚፈራውን በርቦርን በመባል የሚታወቀው የፈረንሳይ ነገስታት ዘሮች ቢሆኑም የፀሀዩ ንጉስን ዙፋን
ቢወርሱም ፣ ድርጊታቸውና በስልጣን መባለጋቸው ፣ የሀገሪቱን ግምጃ ቤት ማራቆታቸው የአያታቸው ገናና ስምና ተወዳጅነት ሊያድናቸው
አልቻለም ። በዚህ ምክንያት በምእራቡ አለም የመጀመሪያው የሆነው
የፈረንሳይ አብዮት እ.ኤ.አ. በ1789 ሊካሄድ
ችሏል ፣ ከዚህ በኋላም ለተወሰኑ ጊዜያት ዘውዱን ለመመለስ የተሞከረ ቢሆንም ፣ የበርቦን ዘሮች ዳግመኛ ወደ ፈረንሳይ ዙፋን ሳይመጡ
ቀርተው ከታሪክ ገፅ ተወግደዋል ።
አንዳንድ መሪዎች ለተከታዮቻቸው እኔ እምለውን አድርጉ እንጂ እኔ እማደርገውን
አታድርጉ ላሉ ይሁን እንጂ ተከታዮች መሪያቸው የሚያደርገውን ማንኛውንም ነገር ያያሉ ፣ ከሚናገረውም ነገር ጋር ያስተያዩታል ።
ስለዚህ እኔ የምናገረውን ብቻ አድርጉ ፣ የማደርገውን አትዩ ወይም የማደርገውን አታድርጉ የሚለው አያስኬድም ። ይህ ብቻ ሳይሆን
በተከታዮቹ ዘንድ ያለውን አመኔታም ክፉኛ ይሸረሽርበታል ። ሌላው ደግሞ መሪዎች በአንድ ዘርፍ ትክክለኛ ነገርን እያደረኩ ስለሆነ
፣ በሌላኛው ዘርፍ ባበላሽም ፣ ብሳሳትም አትጠይቁኝ የሚል አቋም ያላቸው መሪዎች አሉ ። ለምሳሌ የአፍሪካ መሪዎች ምጣኔ - ሀብቱን እያሳደኩ ስለሆነ በዲሞክራሲ ወይንም በሰብአዊ መብት ጉዳይ ምንም አይነት ጥያቄን አትጠይቁኝ ሊሉ ይችላሉ ። ነገር
ግን ይህ አዋጪ መንገድ አይደለም ፣ ምክንያቱም በአንድ ዘርፍ ትክክል መሆን በሌላ ዘርፍ ስህተትን ወይንም እማይደረገውን ነገር
እንዲያደርግ እድልን አይለጠውጠውም ።
ጦርነት የእርስ በእርስ ጭቃ መቀባባትን የሚያስከትል አስቀያሚ ነገር ሲሆን
፣ በአካላዊ ብቻ ሳይሆን በስነ- ልቦናም ጭምር የሚያደርሰው ጉዳት ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ፣ ከጉዳቱም ለማገገም አመታትን ይፈጃል
። ጦርነት የፖለቲካ ልዩነት ተቀጥላ ሲሆን በክላውሽዊትዝ እንደተገለጠው
ይህ ብቻ ሳይሆን ፣ በአሸናፊነት ለመወጣት ጦርነት ፍትሀዊ መሆን አለበት ። ጥሎት የሚሄደው በቀላሉ የማይሽር ጠባሳና ሰቀቀን (Trauma) እንዲሁ ከባድ ከመሆኑ የተነሳ የሚያደርሰው
መናጋት ከፍተኛ ስለሚሆን በአመታት ውስጥ በቀላሉ የማይሽር ነው ። አንዱ የመሪው ስራ የግጭት ፍንጮችን በማየት ፣ ገና ብቅ ሲሉ
መስተካከል የሚችሉትን ማስቀረት መቻል ነው ። በጣም አስፈላጊ ካልሆነና ማስቀረት የማይቻል ካልሆነ በስተቀር ወደ ግጭት ሊገባ የሚችልበትን
መንገድ በሚችለው አቅሙ ማስቀረት መቻል አለበት ።ይህ ብቻ ሳይሆን ጦርነት ንፁሀን የሆኑ ነገር ግን የጦርነቱ ሰለባ የሚሆኑ ሰዎችን
ይፈጥራል ። በጦርነት ውስጥ በሁሉም ወገኖች አስፈላጊ ከሆነው በላይ
እርምጃ የመወሰድ አደጋም አለ ።