በአለም ላይ ረጅም ታሪክ ያላቸው ብዙዎቹ ሀገራት በአሁኑ ውስጣዊ
ሰላምና መረጋጋት ያላቸው አይደሉም ። መካከለኛውን ምስራቅ ብንወስድ የሰው ልጅ ስልጣኔ የጀመረበት ፣ በርካታ የአለም ሀይማኖቶች
የፈለቁበት ሆኖ ሳለ በአለም ላይ በአሁኑ ሰአት እጅግ ሰላም የራቀው ክልል ሆኖ፣ በዛ ክልል የሚነሱ ውዝግቦች ለተቀረው አለምም
አስፈሪ እስከመሆን ደረጃ የደረሱ ናቸው ። ለምሳሌ ኢራቅን ብንወስድ የሰው ልጅ ስልጣኔን ጀምሮበታል በሚባለውሜሶፖታሚያ፣ የባቢሎን
ስልጣኔ እምብርት የነበረች ስትሆን በአንፃሩ ግን በታሪኳ እጅግ አሰቃቂ ጦርነቶች ፣ በአለም ላይ ይህ ነው እማይባሉ አምባገነኖችን
፣ ከዚያም የኢራቅ - ኢራን ፣ የኢራቅ - ኩዌት ጦርነትን ፣ ብሎም በሀያሏ አሜሪካ እስከ መወረር ጭመር የደረሰች ሀገር ነች ።
ጊዜና ታሪክ አንድ ሲሆኑ ፣ ታሪክም ሆነ ጊዜ ምህረት የላቸውም
። ብድግ ያደረገ ታሪክ መልሶ ወደ ታች ሲያወርድ ፤ አንድ ሰው መጥፎ ነገርንም ቢያደርግም ታሪክ ምንግዜም ቢሆን እያነሳ ሲጥለው
ይኖራል ። የጊዜ ጎማ በማይቆም ሁኔታ በተሽከረከረ ቁጥር ፣ ጊዜም ይዞት የማይመጣው ነገር የለም ። ሰዎች ባንድ ጊዜ ተነስተው
ሰማየ ሰማያት ይደርሳሉ ። ትንሽ ቆይቶም ከደረሱበት ተመልሰው ወደ ታች ይወርዳሉ ። ጥሩም ፣ መጥፎም እንዲሁም የምንፈልጋቸውንም
የማንፈልጋቸውም ነገሮች ሁሉ ጊዜ ብንወድም ባንወድም ይዟቸው ይመጣል ፣ ይዟቸው ይሄዳል ። ታሪክ ግብታዊ የሆነ ነገር ሲሆን ፣
በመንገዱ ያገኘውን እየገነዳደሰ ፣ አዳዲስ ክስተቶችንም እየፈጠረ የሚጓዝ ሁነት ነው ።
በእስልምና ሀይማኖትም ብንወስድ በርካታ ታላላቅ የሺአ እምነት ቅዱስ
ስፍራዎች እሚገኙት በዚህችው በኢራቅ ነው ። ይህ ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ ከሳኡዲ አረቢያ ቀጥሎ ከፍተኛው የአለማችን የነዳጅ ዘይት
ክምችት እሚገኘውም በዚህችው ሀገር ነው ። በእስራኤልና በፍልስጥኤም ብሎም በአረቦች መሀከል የሚታየውም ለሺ ዘመናት የቆየ አለመግባባት
ከዚሁ ከታሪክ ጋር የተያያዘ ነው ። ስለዚህ ያለፈ ታሪክ ዝም ብሎ ያለፈ ነገር አይደለም ። በአሁኑ አኗኗራችን ላይ ወደድንም ጠላንም
በጎም ይሁን አሉታዊ ተፅእኖ አለው።ረጅምና ሰፊ ታሪክ ያላቸው ሀገራት ታሪካቸው በርካታ ጫናንና ተፅእኖን ያሳድርባቸዋል ። ከድሮው
ታሪካቸው ተፅእኖ ወተው አዲስ ማህበረሰብን መገንባት ትልቅ ብልህነትናንና ችሎታን እንዲሁም ካለፈው አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ነገር
ራስን ማላቀቅን ይጠይቃል ።
እየሩሳሌምን ብንወስድ በታሪክ በጣም አጨቃጫቂ ግዛት ስትሆን እየሩሳሌም
በትክክል የማን እንደሆነች የማይታወቅ ሲሆን በርካታ ይገባኛል ባይ
ወገኖች ሲኖሩ ፣ በዛ አካባቢ የተነሱ ሁሉም ታላላቅ ሀይማኖቶች በሙሉ እየሩሳሌም ትገባናለች፣ የኛ ነች የሚሉ ናቸው ። በታሪክም
ብንወስድ እየሩሳሌም በሮማውያን ፣ በኦቶማን ቱርኮች ፣ በግብፆች በባትርነት ፣ በአረቦች ፣ በማምሉኮች ፣ በመጨረሻም በእንግሊዞች
ቁጥጥር ስርውላ የተገዛች ሲሆን በእነኚህ ሁሉ ሺ ዘመናት ባለቤቶቿ ሲቀያየሩ ቆይተዋል ።
የእየሩሳሌም ችግር በእስራኤል አልፎ የአለም ሀያላንንም ጭምር ያነካካና
፣ እሳት ውስጥ የከተተ ሲሆን አሜሪካ ለእስራኤል በጭፍን ለበርካታ አመታት ድጋፍን ስትሰጥ መቆየቷ ከአረቡ አለም የከረረ ተቃውሞንና
፣ ጠላትነትን ያፈራላት ሲሆን ከአልቃኢዳ በአካባቢው ለሚገኙ ለሌሎች አክራሪ ሀይሎች መፈጠር ምክንያት ሆኗል ። ስለዚህ ታሪክ እሚፈጥረው
ውዝግብና ጭቅጭቅ ቀላል አይደለም ። ይህቺ እየሩሳሌም በታላላቅ ቅዱሳን መፅሀፍት ስሟ የሰፈረ ሲሆን የብዙ ሺ አመታት የውዝግብና
የደም መፋሰስ ታሪክ ያላት ናት። አሁንም ድረስ ያ ታሪክ በየቀኑ በዜና ማሰራጫ የምንሰማው ነው ።
የቀድሞዋን ይጎዝላቪያንም ብንወስድ ሀያላኑ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት
ወዲህ የፈጠሯትን ሀገር ራሳቸው መልሰው ነው ከኮሚኒዝም በኋላ መልሰው ያጠፏት ። በጣሊያንና በግሪክ መሀከል ያለችው ይህችው አገር
ጦሷና መዘዟ ለተቀረውም አውሮፓ ሊተርፍ በቅቷል ።
ስለዚህ ታሪክን እምንረዳበት መንገድ በጣም ቁልፍ ሲሆን ፣ የተሳሳተ
ወይም ከወቅታዊ ተጨባጭ እውነታ ጋር አብሮ የማይሄድ የታሪክ አተረጓጎም ለማያባራ ችግርና ፣ ጦርነት ይዳርጋል ። ታሪክን ለመተርጎም
ከዘመኑ ጋር ማነፃፀር ተገቢ ነው ። ምንም እንኳን ሁሉም ነገር አንፃራዊ ነው ማለት ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ ሊያመራ ቢችልም ታሪክን
ለመረዳት ግን ሳይጠቅም አይቀርም ። በአንድ የታሪክ ወቅት የተፈፀመ ነገር ሊወዳደር የሚችለው በዘመኑ ከነበረው አስተሳሰብ እና
ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ነው ።
ታሪክ እንደ አተረጓጎሙ ሲሆን አሜሪካንን ብንወስድ ሰሜን አሜሪካም
ሆኑ ደቡብ አሜሪካ ያሉ ሀገራት የተመሰረቱት በአሜሪካ ህንዶች መሬት ላይ ሲሆን ፣ በደቡብ አሜሪካ ሀገራትን ሜክሲኮን ብንወስድ ህንዶቹ ለተቀረው አውሮፓዊ ጋር በጋብቻ የተሳሰሩ ሲሆን
የሰሜን ነጮች ግን እንደ ላቲን አሜሪካ ሀገራት ከአሜሪካ ህንዶች ጋራ በሰፊው በጋብቻ የተሳሰሩ አይደሉም ። የታሪክ ሰዎች ፖለቲካ ሲያረጅ ታሪክ ይሆናል የሚሉት አባባል አላቸው ። ይህም አሁን
እንደ ታሪክ እምናነባቸው፣ እምንሰማቸው ነገሮች በዘመናቸው ፖለቲካ የነበሩ ናቸው ። ጊዜያቸው ስላለፈና ረጅም ጊዜ ስለሆነው ግን
ወደ ታሪክነት ተቀይረዋል ። አሁንም ወደ አሜሪካ ፣ ካናዳ ወደ መሳሰሉ ሀገራት የሚደረግ ፍልሰት እነኚህ መጤዎች ውለው አድረው
፣ ከጥቂት ትውልዶች በኋላ ሀገራቸው እንደሚሆን መገመት ይቻላል ።
ያ ታሪክም በአንድ ዘመን የተካሄደ ጦርነት ቢሆነም ሁለት ጎራዎች
አሉት ማለት ነው ። እነኛ ሁለት ጎራዎችም ያንን የታሪክ ሂደት በየራሳቸው መንገድ እና አተረጓጎም ይተረጉሙታል ። ይህንንም በሚፅፏቸው
መፅሀፍት ፣ በሚሰሯቸው ፊልሞች በመሳሰለው በየራሳቸው መንገድ ያንፀባርቁታል ። ለምሳሌ አይሁዳውያን በሁለተኛው የአለም ጦርነት
ወቅት በናዚዎች በደረሰባቸው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ለአለም ለማሳየት እጅግ በርካታ መፅሀፍትን ፣ ፊልሞችን ፣ በአለም ተወዳጅ የሆነው
የአና ማስታወሻ በሚለው ተነባቢ በሆነው መፅሀፍ ጭምር ይህንን በአይሁዳውያን ላይ የደረሰውን ሰቆቃ እሚያሳዩ ናቸው ።
በሀገራችን ሁኔታ ስናየው በጣም ረጅም ታሪክ ያለን ሆነን ነገር ግን ከአለም ከመጨረሻ ድሆቹ ተርታ መሰለፋችን ታሪካችን ይጫነናል ፣ በማለት የተገለፀው ትክክለኝነት ያለው ሲሆን ፣ ያለፈውታሪካችን ረጅም እንደመሆኑና ብዙ ውጣ ውረዶችን ያሳለፈ እንደመሆኑ በነኛ ሁሉ በሺ ለሚቆጠሩ አመታት የተደረጉና የሆኑ ነገሮች በሙሉ ብናምነውም ባናምነውም በኛ ላይ የራሱ በጎም ይሁን አሉታዊ ተፅእኖ አለው።ያለፈ የረጅም ጊዜ ውዝግብ የበዛበት ያሳለፉ ያለፈው ነገር ሲያቃዣቸው (Haunt) እና ሲያስደነብራቸው ፣ ሲያተራምሳቸው ይታያል ።
ታሪካቸው አጭር የሆኑ ሀገራት ስለ
ታሪካቸው ያን ያህል ውዝግብ የለባቸውም ። አሜሪካንን ብንወስድ እንደ ሀገር ከተመሰረተች ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ተላቃ ከእ.ኤ.አ. 1776 ጀምሮ
ወደ 250 አመታት
የሚጠጋ ጊዜ ነው አለምን በነፃ ሀገርነት የተቀላቀለችው ። የአሜሪካን አህጉር የተገኘበትን ጊዜ እንኳን ብንወስድ 500 አመት
ያክል ነው ።
ለአንድ ሀገር ያለፈ ታሪክን መጥቀስ ከችግር አያድነውም ፣ ውስጣዊ መረጋጋት እና ሰላምና ባ ለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ፣ ለምሳሌ የሱዳንን ብንወስድ በአፍሪካ በቆዳ ስፋት ሰፊ ሀገር ሆና ሳለ ነገር ግን በተለያየ አካባቢ ያለውን ክልሏን በልማት በኩል በመዘንጋቷ ምክንያት የመገንጠል እንቅስቃሴዎች በመነሳታቸው በዳርፉር ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ሲያመራ ፣ ደቡብ ሱዳንም የራሱን ነፃነት አውጇል ። ይህም በልማት በኩል እነኚህ ክልሎች ለበርካታ አስርት አመታት ተዘንግተው የኖሩ መሆናቸው ዋናው ምክንያት ነው ። የልማት ትስስርን መፍጠር ለአንድ ሀገር አንድነት ዋስትናን የሚፈጥሩ ነገሮች አንዱና ዋናው ነው ።
እዚህ ላይ ስለትውልድም ይነሳል ፣ ማንኛውም ትውልድ የራሱ የሆነ ታሪካዊ ግዴታ ያለው ሲሆን ወጣቱ ትውልድም የራሱ የሆነ ታሪካዊ ግዴታና ጥሎት ሊያልፈው የሚፈልገው አላማና ግዴታ ይኖረዋል ።
የነቃ የበቃ ፍፁማዊ አገዛዝ «ኢንላይትንድ አብሶሊዩቲዝም» እንደ ፍሬደሪክ ታላቁ የሚባለው የቀድሞዋ የፕሩስያ ንጉስ የነበረ ሲሆን ፣ ይሁን እንጂ በታሪክ በተደጋጋሚ እንደታየው የዚህ አይነት የመሪነት ብቃት ያላቸው ነገስታት ብዙዎች አይደሉም ፣ በዚህ ምክንያትም ከፈረንሳይ አብዮት የጀመረው በርካታ የአውሮፓ ነገስታትን ሲሽር የተቀሩትን እውነተኛ ስልጣን አልባ አድርጓል
።
ይሁን እንጂ እነሱ ጋ ታሪካቸውም በአንፃራዊነት በጣም አጭር ሲሆን ፣ ብዙም ውዝግቦችም የሉበትም ። ስለዚህ እንደኛ ያለፈው ታሪካቸው ሲጫናቸውና ወቅታዊ በሆነው ህልውናቸው ላይ አሉታዊ ተፅእኖን ሲያስከትል አይታይም ።
መሪዎችና መንግስታት እንደምናስበው በአንድ ሀገር ላይ በጣም ትልቅ ተፅእኖ ያላቸው አይደሉም ። ለምሳሌ በጣም በረጅም ጊዜ ሲታሰብ በአንድ ወቅት በስልጣን ላይ የነበረ መንግስት ፣ ከዛ ሀገር መነሾዎችና በመቶዎች በሚቆጠሩ አመታት ውስጥ ተፅእኖው ወይም ትቶት የሚያልፈው አሻራ እንደምናስበው አይደለም ። ያ ብቻ ሳይሆን መሪዎች የሁሉም ነገር አዛዦችና እንደሚፈልጉት መለወጥና መቀየር ይችላሉ ብለን እንደምናሰውበው አይደለም ። እንደ ሰው እንደ ማንኛውም ሰው ውሱንነት አለባቸው ።